1.
አንድን ነገር ሽቼ ደጅ ጠናለሁኝ
ፈቃድህ ከሆነ በዓይንህ ተመልከተኝ
ያቺን ብሩክ እጅህን ዘርጋብኝ
እንባዬን አይተህ ጌታ
ለቅሶዬን ሰምተህ ጌታ
መሻቴን ስጠኝና ኢየሱስ ላመስግንህ (2x)
2.
አንተን ተስፋ አድርጌ በቃልህ ፀንቼ
መልሴን አጠብቃለሁ በተመስጦ ሆኜ
ታማኝነትህን ተማምኜ
3.
በጐ ስጦታና ፍፁም በረከት ሁሉ
ከብርሃናት አባት ከላይ ይወርዳሉ
ከዙፋንህ ይንቆረቆራሉ
4.
መራራነቴ ያብቃ እሾህነቴም ያብቃ
መፈራረሴም ያብቃ በአንተ ፀጋ ልገንባ
ጐስቋላነቴን ጌታ ሆይ እንካ