1.
የምድረ በዳው ድምጽ የአዋጅ ነጋሪው ቃል
መንገዱን ጥረጉ አስተካክሉ ይላል
ክብሩ ይገለጣል ኮረብታው ዝቅ ይበል
ሥጋ ለባሽ ሁሉ እግዚአብሔርን ያያል
እኔ ነኝ ተራራው ትልቁ እንቅፋት
የሕዝብህ ጉስቁልና የድካሙ ምክንያት
ኦ ምንኛ ይመራል የትዕቢቱ ፅዋ
ጌታ ሆይ ዝቅ አርገኝ ሳይገለኝ ፍሬዋ
2.
ጌታ ትዕቢተኛውን እጅግ ይቃወማል
ለትሁታኑ ግን ፀጋውን ይሰጣል
ለስም አገልጋይ ነኝ ፀጋ ግን ያንሰኛል
የእኔ ዝና ወጥቶ የአንተ ተሰውሯል
3.
ኦ ምን ይሻለኛል ጌታ ሆይ ቶሎ ና
ሰዎች አንተን ሊያይ ከቶ አልቻሉምና
የልቤን ኮረብታ ተራራውን ናደው
ፍሬም እንዲመጣ ቅንጣቱን ግደለው