ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #16 / Song #16

ኑ ግቡ ወደ መርከቡ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
ኑ ግቡ ወደ መርከቡ
ጥፋቱ ይኸው እየመጣ ነው
በሩም ለናንተ ነው የተከፈተው
ፈጥናችሁ ግቡ የምህረት ሰዓት ሳያልፍባችሁ
1.
በነፍሳችሁ ላይ አትቃለዱ
በሩ ሳይዘጋ ኑ ወደ መርከቡ
የህይወት ጉዳይ ነው ምክንያት አትስጡ
ከጥፋት ስፍራ ቶሎ ኑ ውጡ
2.
እጁን ዘርግቶ የሱስ ሲጠራህ
የፍቅር ጥሪውን ና ልጄ እያለህ
እምቢ የምትል ዛሬ ግን መስሎህ
ተው አትጨክን ና ወደ አምላክህ
3.
ድቅድቅ ጨለማ የሚሆንበት
ከሰው ልጆች ደስታ የሚጠፋበት
የምሬት እምባ የሚፈስበት
ጊዜው ሩቅ አይደለም እናስብበት
4.
እንደኖህ ዘመን የዛሬም ሰዎች
ጥፋት የታለ እናንት ግን ሞኞች
ሲሉ ሲያፌዙ ባመፀኝነት
ድንገት ሊይዝ ነው ያ የጭንቅ ሰዓት
5.
የመርከቡ በር በአምላክ እጆች
ቶሎ ሳይዘጋ እላንት ግን ሰዎች
በመንታ ሀሣብ አትዋልሉ
ወስኑና ግቡ ወደ መርከቡ
100%
100%