ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #285h / Song #285h

ስማ መላእክት ዘመሩ

Hark! The Herald Angels Sing

ምድብ / Category: ልደት / Christmas
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ስማ መላክት ዘመሩ
ክብር ላምላክ እያሉ
ሰላምም በምድር ላይ
ኃጥዕ አምላኩን እንዲያይ
2.
ነገዶች በደስታ ቃል
አሁን እልል እንበል
ንገር ከመላእክት ጋር
ክርስቶስ ጌታ ተወልዷል
ስማ መላእክት ዘመሩ
ክብር ላምላክ እያሉ
3.
ሰማያት ይስገዱልህ
ክርስቶስ አንተ ጌታ ነህ
በበረት የተወለድህ
መላእክት ዘመሩልህ
ሰላም በምድር ለሰው
ለደካሞች ዕረፍት ነው
4.
ጌታ በምድር ተወልዷል
ክርስቶስ የኛ አማኑኤል
ስማ መላእክት ዘመሩ
ክብር ላምላክ እያሉ
5.
አንተ የሰላም መስፍን
የጽድቅ ፀሐያች ነህ
ሕይወትና ብርሃንን
በክንፎችህ አብራልን
ክብሩን በሰማይ ትቶ
ፍጡር እንዳይቀር ሞቶ
6.
የሰውን ልጅ አስነሣው
ዳግም ልደትን ሰጠው
ስማ መላእክት ዘመሩ
ክብር ላምላክ እያሉ
100%
100%