ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #9 / Song #9

ሰናክሬም ጦር አሰልፎብኝ

God is Good all the time

ምድብ / Category: ልደት / Christmas
ደራሲ / Author: ተመስገን
ዓመት / Year: 2019
👁️ Views: 7
ምስጋና (2) መልካም ነው ዝማሬ(2)
እሰዋለሁ ለአምላኬ እልልታን ጨምሬ
ለጌታ ሰግደትን ጨምሬ
1.
ሰናክሬም ጦር አሰልፎብኝ
የማደርገው ምንም ሲጠፋኝ
የምስጋና መዝሙር ለጌታ
ስዘምር ጠላቶቼን መታ
2.
[የድልድይ ግጥም እዚህ ያስገቡ]
3.
2. ሌሊቱን በሙሉ ስለፋ
አንድም የሚያዝ ዓሣ ጠፋ
ታንኳዬን ለጌታ ስሰጠው
መረቤን በአሣዎች ሞላው
4.
3. ጳውሎስና ሲላስ በእስር ቤት
ተጥለውም ሳሉ በእስራት
መዝሙር ሲዘምሩ ለጌታ
የእጃቸው ሰንሰለት ተፈታ
5.
4. ክፉ ሰልጥኖበት ሳዖል ላይ
አዕምሮውን ስቶ ሲሰቃይ
ዳዊት በገና ሰደረድር
ክፉው መንፈስ ሸሸ ሲዘመር
6.
5. ሁሉን ለሚችለው ለኢየሱስ
በእምነት አስረክቦ መፈወስ
በምስጋና ሆኖ መቆየት
ባርኮት ይመጣል ከጸባኦት
100%
100%