ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #280h / Song #280h

ኦ ቅዱስ ሌት

O Holy Night

ምድብ / Category: ልደት / Christmas
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ኦ ቅዱስ ሌት
ከዋክብት ያበራሉ
ያዳኛችን ልደት ስለ ሆነ
ዓለም በኃጢአት ውስጥ ስትጨማለቅ
መጣላት ተስፋዋን
ስትጠብቅ
2.
ግሩም ተስፋው ነፍሶችንም ያረካል
ደስ ይበለን ንጋት ሆልናል
ስገዱለት የመልአኩን ድምፅ ስሙ
በቅዱስ ሌት በክርስቶስ ልደት
ቅዱስ መዝሙር ለርሱ ቅርቡለት
3.
በእምነት ኃይል በብርሃኑ ተመርተን
በደስታ ልብ እንይ ያንን ሕፃን
የኮከቡን ብርሃን አይተው ሲሮጡ
ጥበበኞች ከሩቅ
ሀገር መጡ
የነገሥ ታት ንጉሥ
በበረት ወድቆአል
4.
በችግርም ወንድማችን ሆኗል
የኛን ሐሳብ ድካማችንን ሁሉ
እርሱ ያውቃል ወድቀህ ስገድለት
ያንተ ንጉሥ ተወልዷል በበረት
5.
ነግሮናል አንዱ አንዱን እንዲወደው
ሕጉ ፍቅር ወንጌሉም ሰላም ነው
ነፃ ወጥቷል ባሪያም ወንድማችን ነው
በርሱ ስም ጭቆና ሁሉ ጠፍቷል
6.
ስለዚህ ኑ በደስታ እንዘምር
ቅዱስ ስሙም በውስጣችን ይክበር
ክርስቶስ ጌታን አክብረው ለዘላለም
ስልጣኑንም አስታውቅ ለዚች ዓለም
ኃይሉን ስሙን አውጅ ለዘላለም
100%
100%