1.
ስንቱን አለፍክ ከእርሱ ጋራ
በሸለቆ በተራራ
ታዲያ ዛሬ ምን ሆነህ ነው
ጌታን ውስን ያደረግኸው
የሱስ ሁሉን ቻይ ነው
ይቻለዋል አዎን ይቻለዋል
ለየሱስ ምን ይሳነዋል ሁሉ ይቻለዋል
2.
በታላቅ ድምጽ ጌታን ጠርተህ
እርሱም ሰምቶ ፈጽሞልህ
ስታወድሰው የነበርከው
ኧረ ዛሬ ምን ሆነህ ነው
እምነትህ የጠፋው
3.
ዮርዳኖስን አልፈህ ወጥተህ
ዛሬ ምነው ዛለ ልብህ
ተበራታ ጌታን ተመን
ይቻለዋል ሊያደርግ ሁሉን
ሊያቃልል ችግርን
4.
ብዙ አይተህ ብዙም አልፈህ
ዳገት ወጥተህ ቁጥቁል ወርደህ
ታዲያ ዛሬ ምን ሆነህ ነው
ልብህ የሚጠራጠረው
እባክህ ታመነው