ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #48 / Song #48

ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ወንጌልን ለፍጥረት ስበኩ
እስከዓለም ፍፃሜ ከእናንተ ጋር አለሁ /2/
1.
የነገርኳችሁን ሁሉ እያሳሰባችሁ
ቃሌን እንዲያደርጉ ደግሞ እየመከራችሁ
ከጨለማ ይውጡ ሂዱ ብርሃን አብሩላቸው
የሚቅበዘበዙ ደግሞ እጅግ ብዙ ናቸው
2.
በዲያብሎስ ግዞት ታስረው ሁሌ ሚዋልሉ
ኑሮ መሮባቸው ዛሬ የት እንሂድ የሚሉ
ኣሉና ድረሱላቸው ቃሌን ንገሩአቸው
ሰላምና ደስታ የሱስ ዕረፍት ነው በሉአቸው
3.
ተስፋ ቆርጦ ዛሬ ሞቱን ሁሌ የሚጠብቅ
ህይወትን የሚያድስ አምላክ እንዳለ የማያውቅ
መንገድና ሕይወት እውነት ኢየሱስ ነው በሉት
ታጥቃችሁ ሂዱና አሁን ወደ እኔ መልሱት
100%
100%