ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #40h / Song #40h

እንስገድ ላምላክ

O Worship the King

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
እንስገድ ላምላክ ለክብር ጌታ
እንዘምርም ፍቅሩን በደስታ
መጠጊያ ጋሻችን ፈጣሪያችን
ግርማን ተላብሷል
እንዲሁም መስጋናን
2.
ኃይሉን አስታውቁ ደግሞም ጸጋውን
ዙፋኑ ጠፈር ልብሶቹም ብርሃን
ቁጣውን በነጐድጓድ ድምፅ ያሰማል
በበረታ ሞገድ ኃይሉን ያሳያል
3.
ተነግሮ አያልቅ ያንተ እርዳታ
ሊገኝ ይችላል በሁሉ ቦታ
ከሰማይ በረከትን ለምታፈስ
ለቸር አምላካችን ምስጋና ይድረስ
4.
እኛን ደካሞች ያፈር ልጆችን
ያላንተ ብርታት ተስፋ አይኖረንም
የአንተ ርህራሄ ጸንቶ ይኖራል
ለሰዎችም ሁሉ ተስፋ ይሰጣል
100%
100%