ማራናታ ማራናታ(2)
አሜን ጌታ እየሱስ ቶሎ ና (2)
1.
ባለተሰማ ቋንቋ ልናገር
ከቅዱሳኖች ጋር ልዘምር
ይሄ ነው ናፍቆቴ ቶሎ ና
ውዴ ሆይ ኩራቴ አንተ ነህና ኦሆ
2.
አዲሱን ነጭ ልብሰ ለብሼ
የታረድከውን በግ ዳስሼ
ይሄን ለማየት ነው ናፍቆቴ
እባክህ ቶሎ ና አባቴ ኦሆ
3.
የምድር ኑሮዬ ከአንተ ጋር
ጠቅሞኛል ጌታዬ ይኸው ልናገር
ግን አሁን ናፍቆቴ ይሄ ነው
ማራናታ ጌታ ነው የምለው ኦሆ
4.
ሕዝቡን ከኃጢአት ለሚያድን ለሚፈውስ
ድንቅ መካር ኃያል ስሙም ኢየሱስ
የእስራ ኤል መሪ ታላቁ መስፍን
በቤተልሄም (ተወለደልን) (2)