እግዚአብሔር ነው ታዳጊያችን በጦር ሜዳ መዋጊያችን
በድካም ውስጥ ምርኩዛችን በስደት መፅናኛችን
እርሱን ይዘን የትም ብንወጣ የፈለገው ነገር ቢመጣ
የሱስ ብለን ስንጮህ በእምነት እንወጣለን በአሸናፊነት
1.
በታላላቅ ነገስታት ፊት
ስንከበብ በጠላት ሠራዊት
ኢየሱስ ብለን በእምነት ስንጠራ
ጠላት ብትን ይላል እንዳቧራ
2.
ከየአራቱ ማዕዘናቱ
ቢያስጨንቀንም ጦርነቱ
ብርቱ ስለሆነ ታዳጊያችን
ያለመጠን ሰፍቷል ድንበራችን
3.
ከግራ ከቀኝ ከዚህም ከዚያ
ቢያዋክበን ያለም ውጊያ
ሁሉን በጌታ ችለን አልፈናል
ለምጽአቱ ዋዜማ ደርሰናል