ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #88t / Song #88t

ክብር ለኢየሱስ ይሁን

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
በቀራንዮ መስቀል ላይ በደዌ የደቀቀው
ነፍሱን ስለ ኃጥያቴ መስዋዕት ያደረገው
የሞትን ቀንበር ሰብሮ እኔኑ ሊያወጣ ነው
ማዳኑን ቀምሻለው ምን አለ የምመልሰው (2x)
ክብር ለኢየሱስ ይሁን
አየን አሸናፊነቱን
ኃያል እንደ እርሱ የለም
ይንገሥ ለዘለዓለም (2x)
2.
የተናቀ ደካማ ቢመስልም አመጣጡ
ከእሴይ ልጅ ከዳዊት ሥር የወጣው ቁጥቋጡ
ኢየሱስ አሸነፈ ፍሬው ምድርን ሸፈነ
የእግዚአብሔር ፈቃድ በእጁ ተከናወነ (2x)
3.
በደሙ ኃይል ጸደቅን በሥሙ ድል አገኘን
ማነው የሚቋቋመን ማንስ ነው የሚገታን
እንገሰግሳለን አሸናፊውን ይዘን
ወደ ቅድስቷ ሃገር በድል እንገባለን (2x)
4.
ክብር ምሥጋና ይዘን ከፊቱ እንቀርባለን
በዙፋኑ ላይ ላለ እንሰግድለታለን
ሁሉን የረታ ጌታ ንገሥ እንለዋለን
አቤት ለዘለዓለም እርሱ ኃያል ነው አሜን (2x)
100%
100%