1.
ጌታን ሲጠብቅ ታምኖ የኖረ
ብርሃንን ሳያይ ማነው የቀረ
የነፍስ ጥማት ናፍቆትን ሁሉ
ፀንተህ ብትቆይ መልስ ያገኛሉ
የጉስቁልና ዘመን ያልፍና
ችግር ስቃይ ይታሰብና
ጌታ ዳግመኛ ይጐበኝሃል
አዲስ ሰው አርጐ ይለውጥሃል (2x)
2.
ተረስቻለሁ ተጥያለሁኝ
ለምንም ነገር የማልጠቅም ነኝ
ለምን ትላለህ ጌታ ያስብሀል
በእራሱ ጊዜ ከፍ ያደርግሃል
3.
የኤልያስ አምላክ ወዴት ነህ በለው
በፍፁም ነፍስህ ተግተህ ፈልገው
ከቶ የማይደክም የማይታክተው
የአባትህ አምላክ ጌታ እግዚአብሔር ነው