1.
የሱስ ክርስቶስ ተነስቷል ሃሌሉያ
የድል ቀን ተዘጋጅቷል ሃሌሉያ
በመስቀል የሞተልን ሃሌሉያ
ከጥፋት ሊያድነን ሃሌሉያ
2.
በምስጋና እንዘምር ሃሌሉያ ለንጉሣችን ክብር ሃሌሉያ ስቅለት ቀብርን ታገሰ ሃሌሉያ እኛን ገዝቶ ፈወሰ ሃሌሉያ
3.
በተሸከመው ስቃይ ሃሌሉያ አገኘን መድኅን ከላይ ሃሌሉያ አሁን በሰማይ ነግሷል ሃሌሉያ በክብር ተወድሷል ሃሌሉያ
4.
ምስጋና ይሁን ለአብ ሃሌሉያ ወልድን ስላስነሣልን ሃሌሉያ መንፈስን አወድሱ ሃሌሉያ አንድ አምላክን ሞግሱ ሃሌሉያ