1.
የአምላክ ልጆች ደስ ይበላችሁ
ሞትን አሸንፎ የሱስ ተነሥቷል
የከበቡትን ጠላቶች ድል ነሥቶ
በሞት እና በሲኦል ላይ ነገሠ
2.
ያሰረውን የግር ብረት ሰበረ በክብር ሊያኖረን እኛን ለማዳን መላእክትም ለርሱ መዝሙር ዘመሩ አዳኙ ተነሥቷል ደስ ይበላችሁ
3.
አምላክን በመዝሙር አመስግኑት የተሰጠን መንፈስ ታላቅ ነውና ሕይወታችንን በደስታ ለማርካት ተስፋችንን በርሱ እንድናጸና
4.
የሱስ የኃዘንን ጨለማ አጠፋ የሰማያዊ ክብሩን ሊያካፍለን ድል ስለነሣ ደስ ይበላችሁ ሞትን አሸንፎ የሱስ ተነሥቷል