1.
ያ ቀን ይመጣል
በጥዋት ወይ በማታ
ጨለማ ሁሉ የሚሸሽበት ጊዜ
ያን ጊዜ ክርስቶስ
በክብር ይገለጣል
የርሱን ከዓለም ሊወስድ
የሱስ ሆይ እስከ መቼ ነው
የምጻትህን መዝሙር
የምንዘምር ሃሌሉያ
ሃሌሉያ አሜን
ሃሌሉያ አሜን
2.
ምናልባት ቀትር ይሆናል
ወይም ማታ
ጨለማውን በብርሃን ይለውጠዋል
መጥቶ የርሱን
ከዚህ ዓለም ለመውሰድ
በክብር ብርሃን ይታያል
3.
ከዚህ በደስታ ያለሞት
እንሔዳለን
በዚያ ሐገር በሽታ
ፍርሃት የለም
ከዚህ ወደ ሰማይ
እንነጠቃለን
የሱስ ወደርሱ ሲወስደን