1.
ብፁዕ ሌት ቅዱስ ሌት
በሰላም የሞላ
በሕፃኑ በእናቲቱም ላይ
ክብር ታየ ሲወርድ ከሰማይ
ያ ሌት በቤትልሔም
ያ ሌት በቤትልሔም
2.
ብፁዕ ሌት ቅዱስ ሌት
እረኞች ያዩበት
በዙሪያ መላእክት ሲከቡት
እየዘመሩ ሃሌሉያ
ክርስቶስ ለላንት ተወልዷል
ክርስቶስ ለላንት ተወልዷል
3.
ብፁዕ ሌት ቅዱስ ሌት
የአብ ልጅ መድኃኒት
አብ ቅዱስ ፊቱን አበራልን
የፀጋ ቀንም አነጋልን
የሱስን በመስጠቱ
የሱስን በመስጠቱ