1.
በደስታ የጥንት ሰዎች
መሪውን ኮከብ አዩት
በብርሃኑ ተመርተው
እስኪቆም ተከተሉት
እኛም ባንተ ቸር ጌታ
እንድንመራ እርዳን
2.
በደስታ እንደ ሄዱ
ወደዚያች ትንሽ በረት
በፊቱ ተንበርክከው
ሕፃኑን አመለኩት
እኛም ከዙፋንህ ሥር
ወድቀን ይቅርታ እንውሰድ
3.
በበረቱ ውስጥ ሳሉ
አቀረቡ ስጦታ
ከኃጢአት ሁሉ ነጽተን
በተቀደሰ ደስታ
እኛም ያለንን ሁሉ
እናቅርብ ለንጉሡ
4.
ሁልጊዜ ቅዱስ የሱስ
በመንገድህ ጠብቀን
ያለም ነገር ሁሉ ሲያልፍ
ተቀበል ነፍሳችንን
ኮከብ ወደ ሌለበት
ክብርህ በሚያበራበት
5.
በሰማያዊው ሀገር
የለም ምድራዊ ብርሃን
ብርሃናችን ዘውዳችን
አንተ ነህ ፀሐያችን
እንዘምር ለዘላለም
ሃሌሉያ ላንተ ስም