ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #85t / Song #85t

የኃያላን ሁሉ ኃያል

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ሰማይን የሰራ የምድርም ፈጣሪ
በዘለዓለም ዙፋን ለዘለዓለም ኗሪ
ገናናነትህን ሰማያት ያውቃሉ
ምድርና ሞላዋም ይመሰክራሉ።
የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ
የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነህ
የጌቶችም ሁሉ ጌታ ነህ
ባለ ታላቅ ግርማ ኤልሻዳይ ነህ።
2.
በነገስህ ጊዜ ክብርህን ስትለብስ
ለተጠቃው ህዝብህ ፊትህን ስትመልስ
ድንቅ አድራጐትህን በምድር ስታደርግ
በጽድቅህ ስትፈርድ አመጻን ስትጠርግ።
3.
ቃልህን ስትሰጥ በሲና ተራራ
በልጆችህ ሰፈር በበረሃው ስፍራ
በክብር እሳትህ ተራራውን አጤስከው
በመረጥካቸው ፊት ክብርህን ገለጽከው
4.
የተዳፈሩህን የተነሱብህን
ልክህን ሳያውቁ የታጠቁብህን
እየቀጣሃቸው ተረቶች ሆነዋል
ተፈርተህ ተከብረህ አንተ ግን ኖረሃል።
100%
100%