ጠላቴ ሆይ ብወድቅ እነሳለሁኝ
በጨለማ ብቀመጥ እንኳን
እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል
ስለዚህ ስለዚህ በእኔ ደስ አይበልህ
1.
የወይኑ ፍሬ ተለቅሞ እንደቀረው ቃርሚያ
ደርቄ ቆሜያለሁ እኔ ከበረከት በስቲያ
የሃዘን እንጉርጉሮዬን የምሬት ለቅሶዬን
በአምላኬ ፊት እለቃለሁ እንዲያያት ሕይወቴን
2.
በእግዚአብሔር ላይ ኃጥያትን ሰርቻለሁና
ቁጣው ለቅጣቴ ሆኖ ነዶብኛልና
ወደ ብርሃን እስኪያወጣኝ እታገሳለሁኝ
መልሶም እስኪምረኝ ድረሰ ጠብቀዋለሁኝ
3.
በእኔና በአምላኬ መሃል የሚኖረውን ጉዳይ
ኢየሱስ ይፈፅመዋል የመሰረቱ ድንጋይ
ስለዚህ ጠላቴ ወግድ ጌታ ይገስጽህ
አሁንም ቢሆን ልጁ ነኝ ተረዳ ከልብህ
4.
ለዘለዓለም አይቆጣም ምህረትን ይወዳል
የጠላቴን ምኞት ቆርጦ ዕልልታውን ያቆማል
የውርደት ማቄ ተቀዶ ነጭ ልብስ ለብሼ
ዳግም ዘምራለሁ ለእርሱ ክንዱን ተንተርሼ