ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #96t / Song #96t

የኃጢአተኛውን ጥፋት

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ምሕረትና ዕውነት ፍቅር ቸርነት ከሞላው ጌታ
ኃጥዕ በንስሐ ይቀበል ይቅርታ
ማንም እንዳይጠፋ መድህን ሞቶልናል
ክርስቶስ ኢየሱስ ቤዛ ሆኖልናል
የኃጢአተኛውን ጥፋት
እግዚአብሔር መቼ ይወዳል?
የተጣለ ሰው እንኳን ፈጽሞ እንዳይጠፋ
በምክሩ ያስባል በምክሩ ያስባል
2.
ሰው ግን በውድቀቱ
ለምን ተስፋውን ይቆርጣል ቶሎ?
ለምን ይቀናዋል መውረድ አሽቆልቁሎ?
"ጌታን እጠብቃለሁ ቢገድለኝም" ብሎ
በዕምነት የሚቆም አይቀርም ጐስቁሎ
3.
የሚወደውን ልጅ እግዚአብሔር ለጥቅሙ ይቀጣዋል
መክሮ ይገስጸዋል ያስተካክለዋል
በአባትነት ዓይኑ ይመለከተዋል
ሲፍገመገም ቢያየው ፍጥኖ ይደግፈዋል
100%
100%