ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #125t / Song #125t

ከእግርህ ሥር መሆን

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
በብዙ ነገር እንታወካለን
ኑሮ ልንገፋ እንጨነቃለን
በሥጋ በነፍስ እንባክናለን
አርፎ መቀመጥን
ከአንተም አፍ መስማትን
ገና አሁን ተረዳን ሰምቶ መታዘዝን
ከእግርህ ሥር መሆን ግሩም ነው
ቃልህን መማር መልካም ነው
የማይጠፋም እድል ነው ጌታ ሆይ (2x)
2.
ሲሰሙህ ደስ እንደሚልህ ጌታችን
የአውራ በግ ስብ ብንሰጥህ ከእጃችን
ምንም አያረካህ እንደ መስማታችን
የእኛ ብቻ ይሰማ እያሉ መለፍለፍ
መስማትን ያግዳል ተናግሮ አለማረፍ
3.
ደቀ መዝሙርም ሳይሆን ከቶ ሳይማር
እራሱን የሚሾም ከሹመቱ ሲሻር
ብቻውን ሲወድቅ ያለ አንዳች አጋር
ተግሳፅን ያገኛል ጠቢብ አስተውሎ
ልማር አስቀድሜ ሩጫ ይቆይ ብሎ
100%
100%