1.
በህዝቡ ሁሉ የሚሆን
የምሥራች ተነገረ
ታላቅ ደስታ ነው ልደቱ
ይዘምር እስኪ ፍጥረቱ
መጣ በራልን (በራልን)
ጌታ ሊጐበኘን (ሊጐበኘን)
ቤዛ ሊሆንልን
ከኃጢያት እኛኑ ሊያድን
ቃል ሥጋ ሆነና ከድንግል ተወለደልን
2.
ህጻን ተወለደ ለእኛ
በቤተልሔም በረት ተኛ
ለኃጥያተኞች መዳኛ
ሊሆን የበጐች እረኛ
3.
ሥሙ የተመሰገነ
ክርስቶስ ጌታ የሆነ
ተገልጧልና ልዑሉ
ስገዱለት ዕልል በሉ
4.
ተሽቀዳደሙ ኑ እዩት
የሚመስልህ የለም በሉት
አድንቁት እጅግ አክብሩት
ይገባዋል አመስግኑት
5.
በላይ ለእግዚአብሔር ክብር
ለእኛም ሰላም በምድር
ይሁን ብለን እንዘምር
እረፍት አለ መስቀሉ ስር