በኩርነትህን ለምን ሸጥከው
ኢየሱስን ለምን ለወጥከው
ክብርና ገንዘብ ጠፊ ነው
የማይጠፋውን ምረጠው
ጌታ ይሻልሃል ለዘለዓለም ሕይወት የሆነህ (2x)
1.
ለማያጠግብህ እሮጠህ ምናምንቴ ነገር ወደህ ረብ ረድኤት በማይሆነው በኩረነትህን ሸጥከው
2.
ብዙዎች ወደቁ ተጠልፈው በገንዘብ ፍቅር ተነድፈው ብልጽግና ያታልላል ይሁዳ ጌታውን ሽጧል
3.
ሰይፍ ከዋጠው የበለጠ የኃጢአት ዱር ብዙ ዋጠ አንተን የዋጠህ ምንድን ነው ነፍስህን አንቆ የያዘው