ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #109t / Song #109t

ፈቃድህን እንዳደርግ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የልቤን ስፈጽም አምላኬን ሳልፈራ
ለኋለኛው ዘመን ሳከማች መከራ
ኃጢአትን ስዘራ የኖርኩትን ኑሮ
ፀጋህ አሳመረው ሕይወቴን ቀይሮ (2x)
እንግዲህ ጌታ ሆይ እንዳስተውል አርገኝ
በቀረልኝ ዘመኔ ፈቃድህን እንዳደርግ አስተምረኝ (2x)
2.
ፈቃድህን አውቆ መታዘዙ ጠቅሞኝ
ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ሆኖልኝ
መልካም ሥርዓትህን ተምሬ ተምሬ
በእንግድነት ሐገር እዘምራለሁ ዛሬ
3.
ፈቃድህ ድንቅ ነው የፈጸምከው በእኔ
ለዛሬም ለነገም ባንተ ላይ ነው ዓይኔ
በምሄድበትም መንገዴን አሳየኝ
በቀረልኝ ዘመን ፈቃድህን አስታውቀኝ (2x)
100%
100%