ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #192t / Song #192t

ምሥጋና የሚገባውን

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ምሥጋና የሚገባውን
እግዚአብሔርን እጠራለሁ
ከጠላቶቼም እድናለሁ (2x)
1.
የአመጽ ፈሳሽ ሲያስፈራራኝ የሲዖል ጣርም ሲከበኝ
አምላክህ የታለ ሲለኝ ባላንጣዬ ሲያፌዝብኝ
ከመሠረቴ ሊነቅለኝ ቆይ ብቻ ሲል ሲዝትብኝ
የጌታን ሥም እጠራለሁ ከጠላቴም እድናለሁ
2.
የጌታ ኢየሱስ ሥም ለእኔ የፀና ግንብ ነውና
እስከዛሬም እርሱን ጠርቶ ማንም አላፈረምና
በኪሩቤል የሚኖረው ሙሉ ተስፋ ስለሰጠኝ
ታምኜ ሥሙን እጠራለሁ ከጠላቴም እድናለሁ
3.
በጨነቀኝ ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔርን ጠራሁት
ስቅስቅ እያልኩኝ በእንባ የሆዴን ብሶት ነገርኩት
ከዚያም በበቀል ወረደ ከሰማይ አንጐደጐደ
በመብረቁ አወካቸው በፍላጻው በተናቸው
4.
ለጥርሶቻቸው ንክሻ አላደረገኝምና
ከተዘረጋብኝ ወጥመድ ሁሌ አድኖኛልና
አርነቴን ከሚቀማ ከሰይጣን ጋርዶኛልና
ሥሙ ይክበር ሃሌሉያ እያልኩኝ ልኑር በእርሱ ጉያ
100%
100%