በትዕግሥት ፀጥታ በፀሎት ቆይታ
ድል ይገኛል ከጌታ
በትዕግሥት ፀጥታ በፀሎት ቆይታ
መልስ ይመጣል ከጌታ
1.
የበረታ ሰልፍ ሲከበኝ ከኋላ ከፊት
ቆይቼ እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት
እርሱም ዘንበል አለልኝ ሊያዳምጠኝ
እንባዬን በእጁ ጠርጐ ቃሉን ሰጥቶ አፅናናኝ
2.
ነፍስህ ብትራቆት ፍፁም ባዶ ስትሆን
ያለህን አራግፈህ ተዘርፈህ ስታይ ራስህን
ያሳለፍካቸውን ድሎች አስብ ተስፋህ ይለምልም
ተንበርክከህ ብትቆይ ደግሞ መዳሰስህ አይቀርም
3.
ከድካም የበረቱ ሰዎች በድል ያለፉ
ከኢየሱስ በስተቀኝ በላይ የተሰለፉ
መንግሥታትን ድል ነስተው ያንን ምሽግ የናዱ
የፀሎት ሰዎች ናቸው ጠላት ያርበተበዱ