ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #97t / Song #97t

ቤዛ የሆንክልኝ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ቤዛ የሆንክልኝ ጌታዬ
የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ
ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን
ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን (2x)
1.
በወርቅ ይሁን በብር በጥበብ በዕውቀት
የዳነ ማን አለ ከኃጢአት ውድቀት?
ጌታ ሆይ ! አንተ ነህ ጽድቅን ያለበስኸኝ
በምሕረት አማልደህ ከዓብ ያስታረቅኸኝ (2x)
2.
በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ላይ ሥራ
ከዘለዓለም ሞት ዳንኩኝ ከመከራ
በነጻ ታድዬ የጽድቅን ሥጦታ
ምሥጋና እሰዋለሁ ለተቤዠኝ ጌታ (2X)
3.
ብላቴንነቴን ድካሜን ገምተህ
አንተ ብርቱ ጌታ በእኔ ላይ ተገልጠህ
የበረታብኝን ጠላቴን ቀጥቅጠህ
ድል ያጐናተጸፍኸኝ ኢየሱስ አንተ ነህ (2x)
4.
መልካሙን ሥራህን በሕይወቴ ፈጽመህ
እንድትታይብኝ በኑሮዬ ጐልተህ
ይህ ነው ልመናዬ የዘወትር ጸሎቴ
ክብሬ ዕርካታዬ አንተ ነህ ትምክህቴ (2x)
100%
100%