ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #169t / Song #169t

አስብበት

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የፀጋ የምህረት ዘመኑ አብቅቶ
ብርሃን ተሰውሮ የጥሪው ቀን መሽቶ
ሰማያት ተፈተው ምድር ሳትናውጥ
በነበልባል እሳት ጌታም ሳይገለጥ
አስብበት ዛሬ ነገን አትጠብቅ
ራስህን ስትደልል ዘመንህም አይለቅ
ሕይወት ኢየሱስ ነው ሌላስ አታገኝም
አምነህ ድነህበት ታተም ለዘለዓለም
2.
አብሮ ደስ ይበለን ትንሽ ቆይ ስትልህ
ዓለም በለዘብታ እያባበለችህ
ተደላ ትካዜና ቁጭትን ጠብቆ
ሲዖል እንዳትገባ ሳታስበው ከቶ
3.
የእግዚአብሔር ነገር ለፍጥረታዊ ሰው
ሊገባው አይችልም ፍፁም ሞኝነት ነው
ፍጥረታዊውን ሥጋ መንፈሱ ሲሽረው
ያኔ ትረዳለህ መንገዱ ጥበብ ነው
4.
በመንታ መንገድ ላይ ሆነህ ስታማርጥ
ፈጽሞ ላትረካ መንገድ ስትለዋውጥ
ሞት ጥላውን ጥሎ አፍኖ ሳይወስድህ
ጌታን ተቀበለው እርሱ ነው የሚያረካህ
100%
100%