ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #99t / Song #99t

አቤቱ ጌታችን

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
አቤቱ ጌታችን፣ እስኪ እናመስግንህ
ለውለታህ ምላሽ ክበር እንበልህ
ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥረን ሽቶ
ዕምነት ተስፋችንን ሊያጨልም ዝቶ
አምርሮ ቢነሣም እጅግ ተቆጥቶ
ተገዝቶ አየነው በአንተ ድል ተነሥቶ
ስለ ዕምነታችን ስለ ሕይወታችን
የተሟገትክልን ተመስገን ጌታችን
2.
የተጓዝንበትን መንገድ ሊያቋርጥ
ጠላታችን አልፎ እንቅፋት ቢያስቀምጥ
የተመሸገውን ከፍ ያለውን ቅጥሩን
አፈራርሰህ ጣልከው ኢየሱስ ተመስገን
አንተ ቅን የሆነን መንገድ ታቀናለህ
የተዘጋውንም በር ትከፍትልናለህ
3.
የሕዝብህን ስድብ ከምድር አስወግደህ
ከፊታቸውም ላይ እንባቸውን አብሰህ
ራሳቸውን በዘይት በሞገስ ቀብተህ
በምሥጋናቸውም አንተ ትነግሣለህ
ለታናሹ መንጋ በዝቷል ቸርነትህ
ክበር አምላካችን ዘላለም ልዑል ነህ
4.
ግብዣን አዘጋጅተህ በክብር ጠራኸን
በንጉሥ ገበታ ይኸው አስቀመጥከን
በክርስቶስ ኢየሱስ በከበረው ሥፍራ
ነፍሣችን ጠገበች ከሕይወት እንጀራ
ፈቅደን ከልባችን እናመልክሃለን (2)
ለዘለዓለሙም ለአንተ እንገዛለን(2)
100%
100%