1.
በተዘረጋ ክንድ በበረታችም እጅ
በጌታ መዳኑን ከሞት ከሲዖል እጅ
እንደምን ዘንግቶ ሰው ያጉረመርማል
ወንድሙን ለመውገር እጁን ይዘረጋል
ስጋ ነፍሱን ዘርቶ አመጽ አቆጥቁጦ
ትህትና ተረስቶ የትዕቢት ኃይል ፈጦ
ፍቅርን ገደል ከቶ ጥላቻን ለማንገሥ
ጥርሱን ይስል ጀመር ሰው ለመነካከስ
አንተ ግን ጌታ ሆይ ምህረትህን አፍስስ (2x)
2.
ስፍራውን ለቆ ሲሄድ ለመጉደፍ ሲቸኩል
ትህትናውን አውልቆ ለሞት ሲንቀለቀል
እዪት ያንን ዝንጉ ቃል ኪዳኑን ሲያፈርስ
በአመጻው ብዛት ፍቅርን ሲያቀዘቅዝ
3.
አንተን እየፈራሁ ቀኑን ሁሉ ልኑር
ትህትናም አይራቀኝ አልነፈግህ ክብር
እጅህ እንዳይመታኝ አጉል ደፋር ሆኜ
መተረቻ እንዳልሆን በሃፍረት ተከድኜ