ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው የጐደለኝ
በደልን የምቆጥር ነኝ
ጌታ ይቅር ባይ አድርገኝ
መራራ ሥሬን ቁረጥልኝ
በአንተው ፍቅር የጣፈጠ ሕይወት ስጠኝ
1.
ትንቢትና ዕውቀት መገለጥ ቢኖረኝ
ተራራን የሚያፈርስ ዕምነት ሁሉ ባገኝ
በሰዎች በመላዕክት ልሳን ብናገርም
ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም
2.
ፍቅር ይታገሳል ቸርነት ያደርጋል
በእውነት ደስ ይለዋል ዓመጽን ይጠላል
አይቀናም አይመካም ራሱን ያዋርዳል
እየተበደለ ሁሉን ይቅር ይላል
3.
በአመቺ ቦታ ላይ ጠላቱን አግኝቶ
በመልካሙ መንገድ በፍቅር ሸኝቶ
በሰላም የሚሰድ ከሰው ልጆች ማነው?
ዳዊት በዘመኑ ይህን አደረገው
4.
ጠላቶችህ ሳለን ሞትህ ካስታረቀን
በመስቀል ላይ ፍቅርህ ሕይወት ከሰጠኸን
ሕይወት እንድናተርፍ ሰውን ሁሉ ወድደን
በዕውነተኛው ፍቅር ጌታ አጥለቅልቀን