ከአቅምህ በላይ ሆኖ የሚከብድህ
ለመፍታት ከቶ የሚያስቸግርህ
ምን ችግር አለ የሚያዳግትህ
ሁሉን ቻይ የሆንክ ኤልሻዳይ አንተ ነህ
1.
በሁለት ዓሣ በአምስት እንጀራ
አምስት ሺህ አጠገብክ በበረሃው ስፍራ
ዛሬም አይሳንህም ይህንን ልታደርግ
የደካከምነውን በቃልህ ልትባርክ
2.
ለዕብራውያን መናህን ያወረድክ
እውር ያበራህ ሸባን በእግሩ ያቆምክ
ዛሬም አይሳንህም ይህንን ልታደርግ
የዛለውን ጉልበት አድሰህ ልትለቅ
3.
የትኛው ደዌ ለፈውስ አስቸገረህ
የትኛው ኃያል ተቋቁሞ ያዘህ
የኃያላን ኃያል የነገሥታት ንጉሥ
ጠላትህን ረትተህ መንፈስህን አፍስስ
4.
የሁሉም ዓይኖች ወደ አንተ ናቸው
ምስኪኖችህን መጥተህ ታደጋቸው
ነፍሳትን ሁሉ ማዕበሉንም አዛዥ
በመከራ ጊዜ የጻድቃን አጋዥ