1.
የጠላትህን ክስ ሊደመስስልህ
ከዓብ ዘንድ የቆመ ጠበቃ አለልህ
የኃጢአትህን ሸክም ተናዘህ እረፈው
በደሙ ያጥበዋል ለኢየሱስ ንገረው
ደስ ይበልህ ወንድሜ ከሳሽህ ተጥሏል
የኃጢአትህ ዋጋ በጌታ ተከፍሏል
ምህረቱን ተቀበል ኃዘንህን እርሳው
ከንስሐ ወዲያ ልብህን ደስታ ይሙላው
2.
በእድፋሙ ልብስህ ሰውነትህ ተከድኖ
በአፍረት ተውጠህ በደልህ ተጋኖ
ምንም ነገር ቢሆን "ከቶ ተስፋ አልቆርጥም"
ብለህ ተሟገተው "ከፀጋው አልሸሽም"
3.
ጠላትህን ጥሎ እስራትህን ቆርጦ
ክስህን ደምስሶ ፍርድህን ለውጦ
ያ የፍቅር አምላክ ምህረትን አውጇል
ልብስህም እንዲቀየር ትዕዛዝን አውጥቷል