ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #113t / Song #113t

ና ጌታ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ሕዝብህ ይጠብቅሃል ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
መገለጥህ ናፍቆታል ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
እባክህ ናልኝ ሳትቆይ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
ጊዜው አልደረሰም ወይ ? ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! (3x)
ጊዜው አልደረሰም ወይ?
2.
ስምህን ስለወደደች ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
ነፍሴ ስድብን ጠገበች ና ጌታዬ ጌታዬ ሆይ!
ባርኮቷን እያሰበች ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
ዛሬም በአንተ ታምናለች ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
3.
ድካሙ ሳይበረታ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
አርበኛው ሳይረታ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
የተጋዳይ አለኝታ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
በጠላትህ ላይ በርታ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
4.
ጣኦቱ ተሰባብሮ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
ልመልከት ስምህ ከብሮ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
ከጥንት እንደታወቅህ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
ምድር አንተን ትወቅ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ!
100%
100%