ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #124t / Song #124t

መቼ ነው

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ማለዳ እየመጣህ ስታነቃኝ
ጆሮዬን ከፍተህ ስትናገረኝ
በማስተዋል መንገድ ስትመራኝ
ከሕይወት ምንጭ ውኃ ስታረካኝ
ለምልሞ ነበር ሕይወቴ
እንዲህ አልዛለም ጉልበቴ
እባክህ አስበኝ አንተ ነህ መድኃኒቴ
መቼ ነው ነቅቼ ድምጽህን የምሰማው
ለነፍሴ መጐብኘት መጽናናቴ የሚመጣው (2x)
2.
በሌሊት ስነሳ ከእንቅልፌ
ሥምህ ነው የሚመጣው ፈጥኖ በአፌ
ህመሜን ለአንተ እናገራለሁ
ድምጽህን አሰማኝ እማራለሁ
ጌታ ሆይ መቃተቴን ስማ
ነፍሴ እንደዚህ ተዳክማ
እንደ ምን ትዘልቃለች ትካዜን ተሸክማ
3.
የተወሰነው ስዓትህ ሞልቶ
የሀዘኑ ጊዜ አብቅቶ
ድካም ድንዛዜ ተወግዶ
ኃይልህ የሚሞላኝ ከላይ ወርዶ
መቼ ነው ደስ የምሰኘው
በጉብኝትህ የምጽናናው
ጉልበት ተመልሶ በእግሬ የምቆመው
100%
100%