በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር
በከንቱ መታበያችን ይቅር
በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር
1.
በክርስትናችን ዕድሜ ቆጥረን
በልምምዳችን ኮርተን
በትህትና መማሩ ቀረና
እድገታችን ቆመ ታበይንና
2.
ባስተያየታችን ጠቢባን ነን
ትንኝን እናጠራለን
ራሳችንን ማንጻት ሳይቻለን
የሌላውን ጉድፍ እናያለን
3.
ማደጋችንን እዩልን እያልን
በከንቱም እየታበይን
አንተንም በዚህ እያሳዘንን
ሳይታወቀን ስንቶችን ጐዳን
4.
እንደ ሕጻናት የዋሆች አርገን
ንጹህ ልብን መልስልን
ዓይናችንን እየገለጥህ
አንተው አመላልሰን በብርሃንህ
5.
በቃል በስርአት ሙታን ሆነን
በፍቅር እየታነፅን
በእውነት እንደግ ወደ ኢየሱስ
እየታበይን እንደምን እንነስ