እስከዛሬ የጠበከን
ከፍላጻ የሸፈንከን
ዳርቻችንንም ያሰፋህልን
እንባችንን ና አብስልን
1.
በማይገሰሰው ክብርህ
በማይመጠን ጉልበትህ
አንተነትህን ያሳየህ
ለእኛም ከለላ የሆንህ
2.
የጠላትን ቁጣ አይተን
ልካችንን ስንመጥን
ተስፋ ቆርጠን ወየው ስንል
አማኑኤል ደረስክልን
3.
በማባበል ሊያስማማን
ካልተሳካው ሊያስፈራራን
ጠላት ሲዝት ሲያሽካካብን
ሴራውን ያከሸፍክልን
4.
ድብልቅ ኑሮ ያልኖረ
ከእግዚአብሔርም የተማረ
ቢማቅቅም ያሸንፋል
የአምላኩንም ሥም ያስጠራል