1.
በዚች ምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ አለብኝ
አኔ ዝም አላለሁ አንተ ተዋጋልኝ
አንተን ያሰለፉ ስልፉ ሰምሮላቸው
አይቼ ተምሬያለሁ ከድል ዝማሬያቸው
ዝም ብዬ አቆማለሁ
ሰልፉን ለአንተ ለቃለሁ
በእምነት ወደ አንተ አያለሁ ጌታ ሆይ
ድልህን አጠብቃለሁ (2x)
2.
ሰልፉ የእኔ መስሎኝ አረታለሁ ብዬ
በሥጋዬ ስታገል ተዝለፍልፌ ዝዬ
መረታቴ ነው እኮ ኢየሱስ ጌታዬ
ኧረ ቶሎ ናልኝ አይብዛ መከራዬ
3.
የእሳት ሰረገላው መለኮታዊው ጦር
የድምፅህ ነጐድጓድ ጠላት የሚያሸብር
ይምጣ ይዋጋልኝ እኔ ኃይል የለኝም
አሁን አውቄያለሁ ሰልፉ የእኔ አይደለም