ልብህ ጽኑ ይሁን አትላላ ጠንክር
በአመንክበት ጌታ በፍፁም አትፈር (2x)
1.
ተድላና ደስታ መጽናናት በረከት
ሁሌ መንደላቀቅ በተሟላ ሕይወት
እንደዚህ አይደለም እንዲህ አትመልከት
ክርስትና አንዳንዴ መከራም አለበት
2.
የጨለማው ስልጣን ጥላውን ዘርግቶ
ጠላት ኃይሉን ሲያሳይ እጅግ ተቆጥቶ
በበትር ሲመታህ ሆምጣጤ ሲያጠጣህ
በመስቀሉ መንገድ ወንድሜ አይክፋህ
3.
ማምለጫ ስትሻ ቀዳዳ ስትፈልግ
ጭላንጭሉስ እንኳን ሲደፈን ሲመረግ
በወህኒ ተጥለህ ሰው ሁሉ ሲረሳህ
የሕይወትህ ጌታ የሚረሳህ አይምሰልህ
4.
በምስራቹ ቃል በወንጌል ተሟገት
ልብህ ሰፊ ይሁን አርቀህ ተመልከት
ለማያልፈው ርስት ለአገርህ ተዋግተህ
በላይ እንገናኝ ደምህን አጥለቅልቀህ