ኦ ክብር (4x) ሃሌሉያ
ከይሁዳ ነገድ ለሆነው አንበሳ ለሌለው አምሳያ
ልበል ላመሥግነው ከአንጀቴ
ውለታው ስለበዛ ይህ መድኃኒቴ
1.
ሳላውቀው ያወቀኝ ሳልሻው ያዳነኝ
በአስገራሚ ፍቅሩ እኔን የወደደኝ
ከጥፋት ሩጫ ነፍሴን የመለሳት
ኢየሱስ ነውና ያወጣኝ ከእሳት
2.
በልጅነቴ ጊዜ ያኔ በለጋነት
ጠላት ሲጐትተኝ ወደዚያ ባርነት
ፀጋው ባይበዛልኝ እጁ ባይደግፈኝ
የት ቦታ ነበርኩኝ ክንፉ ባይጋርደኝ
3.
ጥሩር ሆኖልኛል በጦርነት ጊዜ
ፍላጻ ሲያቆስለኝ በሃዘን በትካዜ
ውለታውን እያሰብኩ ላመሥግነው ጌታን
አይገኝምና እንደ እርሱ የሚረዳኝ