ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #143t / Song #143t

ምሥጋና ይገባሃል

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ምሥጋና ይገባሃል የሰራዊት ጌታ
ከቶ ማን ተገኝቷል ማኅተሙን ሊፈታ
ምሥጋና ይገባሃል ክብርም ይገባሃል
መወደስ ይገባሃል መንገሥም ይገባሃል
1.
የመጀመሪያውና የመጨረሻው ክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሚመጣው የእግዚአብሔር በግ የታረድከው በደምህ እድፈቴን ያጠብከው
2.
እስራታችንን የበጣጠስከው ቀንበራችንን ደግሞ የሰበርከው አርነታችንን በደምህ ያወጅከው በላይ በአባትህ ቀኝ ያለኸው
3.
ዋጋችንን ልትሰጠን ልታሳርፈን በማይነገር ሀሴት ልታስደስተን በጽዮን ውስጥ እፎይ ልታሰኘን የምትመጣው እኛን ልታጽናናን
100%
100%