ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #152t / Song #152t

ያ ተንከራታቹ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ያ ተከራታቹ ኮብላይ ወገናችን
መቷል እንደገና እሰይ ደስ ይበለን
ያ ተከራታቹ ኮብላይ ወገናችን
መቷል እንደገና እሰይ ደስ ይበለን (2x)
1.
በመዳኑ ምክንያት መላዕክት ፈንጥዘው
በአገልግሎቱም ብዙ ሰዎች ረክተው
ታንጸው በቃሉ እንቅፋት እግኝቶት
ወድቆ የነበረው አዳኙንም ከድቶ
2.
መርዶውን እየሰሙ ሰዎች አልቅሰውለት
ጌታም እንዲያስነሳው ከልብ ጸልየውለት
በመራራ ጩሐት ለአምላኩ ነግረውለት
መልሶ እምጥቶታል እግዚአብሔር አዝኖለት
3.
የውድቀቱን ምክንያት ነግሮ አስጠንቅቆታል
ወንድሞቹ ቀድሞ ጌታ አልቅሶለታል
ተግሳጽ እየናቀ ክወጥመድ ቢገባም
ጌታ ቸር ነውና አልጨከነበትም
4.
ያን ጨካኝ አንበሳን በግልጽ አሳፍሮ
በብረቱ በትር መንጋጋውን ሰብሮ
ዳግም አምጥቶታል እግዚአብሔር ይመስገን
ሙሾው ተለውጧል እሰይ ደስ ይበለን
100%
100%