1.
አብን በዙፋኑ ወልድን በስተቀኙ
በምድር የተገፋውን በክብር ሊገናኙ
ሲጋብዙት ታይቶት ክርስቲያን በጣሩ
ተፈፀመ ብሎ ወጣ ከሃሩሩ
ለረጅም ዘመናት ተቸግሮ ማቆ
ክርስቲያን ተሻገረ ወላፈኑን ዘልቆ
2.
እውር ፈሪሳውያን በምናቸው ይዩ
ፀዳል መፈንጠቁን ከችግር ትይዩ
በመከራ ናዳ በሰዎች ጫጫታ
ሩጫውን አከተመ ጀግናው ሳይረታ
3.
ሃገር ሃገር ሲዞር ሲንከራተት ከርሞ
መልኩ ተቀይሮ በመከራ ከስሞ
ከጅራፍ ከዱላ ከጨካኞች ጡጫ
ክርስቲያን አንቀላፋ አረፈ ከእርግጫ
4.
እንደነ ያዕቆብ በደም ተበክለዉ
ለወንጌል ሊደፉ ለቃልኪዳናቸው
በሰልፍ ቆመዋል ተራ ይጠብቃሉ
ኢየሱስ (3x) ይላሉ