1.
በሰልፉ ሜዳ በዝቶ ጠላቴ
ፍርሃት ሲያርደኝ ፈርቶ ጉልበቴ
ጠፍሁ ብዬ ስል ወየው ጌታዬ
ከፊቴ ያልፋል ኢየሱስ ጋሻዬ
ካፈጠጠብኝ በዓለም ካለዉ
እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው
የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው
ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ነው
2.
ጠላት እንደ ንብ ከቦኝ ቢመጣ
ምሽጌን ትቼ እኔም አልወጣም
በእግዚአብሔር ሥም እሸንፋለሁ
ጐልያድም ወድቆ በዓይኔ አየዋለሁ
3.
ፅኑ ኃያሉ የአምላክ ጦረኛ
አንዱ ለሺህ ነው የእምነት አርበኛ
ከአመፀኞች እጅ ደሙን በትኖ
ፍሬውን ያበዛል በአምላኩ ታምኖ
4.
ረዳት እንዳለኝ ጠላቴም ያያል
እንደ ዘበተ መቼ ይቀራል
የመስቀል ፅዋ እኔም ጠጣለሁ
ድል ይታወጃል አሻገራለሁ