ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #118t / Song #118t

እንደተቀበልኩት ምህረት

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
እንደ ተቀብልኩት ምህረት
እንደ ቸርነትህ ብዛት
እንዳገለግልህ እርዳኝ
ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስህን እሳት
1.
እስራቴን ቆርጠህ ቀንበሬን ሰብረሃል
ነፍሴ እንድታከብርህ ነጻ አውጥተኸኛል
ባርነት አበቃ ልጅ ነህ ብለኸኛል
በደምህ ቃልኪዳን የአንተ አድርገኸኛል
2.
የተፍገመገመ ከውድቀት እንዲተርፍ
የደከመን ሁሉ በቃልህ እንድደግፍ
አንቃኝ በማለዳ ቀስቅሰኝ ከእንቅልፍ
ታማኝ ሎሌ አድርገኝ ልብን የሚያሳርፍ
3.
ስንፍናዬን አርቅ በተግሳፅህ በትር
እንድተጋ እርዳኝ ከፀጋህ ዙፋን ሥር
ኢየሱስ ያድናል ብዬ እንድመሰክር
ሕይወቴን ሙላልኝ በመስቀልህ ፍቅር
4.
ጥበብ ለሌላቸው ለማያስተውሉ
ለተማሩም ሰዎች አውቀናል ለሚሉ
ወንጌሉን ልናገር እንዲድኑ አምነው
ለእነዚህ ሁሉ ዕዳዬ ትልቅ ነው
5.
ወንጌል አይቆጠብ አይወሰን በክልል
እስከ ምድር ዳር ይሂድ ቃልህ ሳይከለከል
ለቅርቡ ለሩቁ ጽድቅህም ይታደል
የሱስን አግኝቶ ፍጥረት እሰይ ይበል
100%
100%