ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #182t / Song #182t

አየሁ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
አየሁ (3x) አሻግሬ አየሁ
አምነው የሞቱትን ልመስል ተመኘሁ
2.
አብርሃምን አየሁ የእግዚአብሔርን ወዳጅ
ይስሐቅን ሊሰዋ ለሰይፍ የሚያዘጋጅ
ቃሉን ያከበረ ያን ቁም ነገረኛ
በሀሳቡም ቁርጠኛ የእምነትን አርበኛ
ስውር ጣዖት የለውም ከአምላኩ የሚነጥል
በቀውጢ ዘመናት እምነቱን የሚያስጥል
3.
ሐዋርያትን አየሁ የፅድቅን ሰልፈኞች
የኃጢአትን ጠሮች የእምነትን ቀንድኞች
በአንድነት ፀሎት ምድርን ነቀነቋት
በድል ብርሃን ወንጌል ባንዴ አጥለቀለቋት
ከጌቶቹ ጌታ ፈቃድ ነበራቸው
ሥልጣናት አልቻሉም ከቶ ሊያግቷቸው
4.
ሰማዕታትን አየሁ እነ እስጢፋኖስን
ዓለም ሲጠላቸው አምነው ኢየሱስን
የደም ጥማተኞች ፍዳ ሲያሳዯዋቸው
ፊታቸው ሲያበራ ያም ሳይበግራቸው
ለዓለም ሲያማልዱ ልክ እንደ ጌታቸው
አቤት ሲያስቀና ያ አሟሟታቸው
5.
ኮብላዮችን አየሁ ከጨለማ ገብተው
ሲዖልና ሰይጣን ጌታም የለም ብለው
በሥሙ ዘብተው በደሙ ቀልደው
የለም ካሉት ጋራ በሞት ተገናኝተው
መንፈሴ አያቸው በአንድነት ሲንጫጩ
በሙታን ዓለም ውስጥ በእሳት ሲወራጩ
6.
እንግዲህ ጌታ ሆይ እኔነቴን ግዛ
ኪዳኔን አጥፌ ሞትን እንዳልገዛ
ብርሃኑ ደብዝዞ ጭጋጉ ሲከበኝ
አንተው እየመራህ ወደ ላይ አዝልቀኝ
የተፃፈው ሁሉ ለትምህርት ሆኖልኝ
በፅናት ታግዬ እንዳሸንፍ እርዳኝ
የተጻፈው ሁሉ ለትምህርት ሆኖልኝ
ገድሉን ተጋድዬ እንዳሸንፍ እርዳኝ
100%
100%