ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #185t / Song #185t

ኃጥያት ሥሩን ሰዶ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ኃጢአት ሥሩን ሰዶ ሳይጠነክርብኝ
ሳይታወቀኝ አድጐ ሞትን ሳይወልድብኝ
ንስሃ እንደገባ በጊዜ ገስፀኝ (2x)
1.
የሌብነት ካባ ወርቁም ሆነ ብሩ
ከድንኳኔ በታች ተቀብረው ሳይቀሩ
ቃልህን ለመጠበቅ ልጆችህ ሲጥሩ
በተደበቀ እርም ወድቀው ሲማረሩ
2.
ኃጢአትን ታቅፌ ጌታ ሆይ ብልህም
ውስጤ ሳይስተካከል ብዘምርልህም
ወይም ብሰብክልህ ጉድለቴን ሳላውቀው
ምን ፍሬ ይገኛል በከንቱ መሮጥ ነው
3.
ጌታ ሆይ የለኝም ከአንተ የሚቀርበኝ
ድካሜን ብርታቴን ተረድቶ የሚያውቅልኝ
ስለዚህ መርምረህ ንገረኝ በደሌን
ንስሃ ልግባ እኔ አዋርጄ እራሴን
100%
100%