ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #10d / Song #10d

አቤት እግዚአብሔር

Alas Lord

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: tM
👁️ Views: 10
አቤት እግዚአብሔር እርሱ አምላክ የሆነው
እንዴት ታደለ ምሥጉን ሕዝብ ነው።
1.
ዓላማ ይዞ የተሰለፈ
ግርማ ሞገሱ አምላኩ የሆነ
መርዛሙን እባብ ረጋግጦት ያልፋል
የጠላቶቹን መንደር ይወርሣል ።
2.
ምድረ በዳውን አለምልሞለት
ጥቂቱን ነገር ጌታ ባርኮለት
በስላም ውሎ በሰላም ያድራል
እግዚአብሔር ህዝቡን እንዴት ወዶታል ።
3.
በረሐብ ዘመን መናን አብልቶ
ጭንቀት ሲበዛ ስላምን ሰጥቶ
ከኋላ ከፊት ሆኖ ከለላ
እርሱ ይመረዋል በድል በተድላ ።
4.
በብርቱ ታምኖ ሁሉን ይረታል
በርሱ ተዋግቶ ምርኮን ይማርካል
አይናወጥም ልቡ ጽኑ ነው
ጋሻ መከታው እግዚአብሔር ነው ።
100%
100%