1.
ከኔ ጋር ሁን በጨለመ ጊዜ
ጨልሟልና ከኔ ጋር እደር
ያላንተ ረዳት በታጣ ጊዜ
የረዳተ ቢስ ረጅ አትለየኝ
2.
የሕይወት ቀን ቶሎ ይቸኩላል
የምድር ተስፋም በቶሎ ያልፋል
በፍጥነትም ሁሉ ይለወጣል
የማትለወጥ ሆይ አትለየኝ
3.
በየሰዓቱ ፊትህን እሻለሁ
ከሐዋርያትህ ጋር እንደነበርህ
እኔን እንደነሱ አትለየኝ
በችግር በደስታ አትለየኝ
4.
በየጊዜው እናፍቅህአለሁ በፀጋህም ድልን አገኛለሁ
ያለ አንተ የሚመራኝ የለም
ማሸነፍ እንዳገኝ አትለየኝ